ማሻ፣ ታህሳስ 17/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ:የሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ እና የሲኖዶስ አባል በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።
ብጹዕነታቸው በቆይታቸውም የሸካ ሀገረ ስብከትን በማቋቋም ለሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እና መንበረ ጵጵስና ግንባታ መሠረተ ድንጋይ እንደሚያስቀሚጡ የሚጠበቅ ነው ።
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሸካ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ:የሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ እና የሲኖዶስ አባልን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ልዑክ ጋር በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በአቀባበል ስነ ስረዓቱ ላይ የየኪ ወረዳ ቤተኪህነት ፣ የአራቱ አድባራት አገልጋዮች ፣ ማህበረ ቅዱሳን የቴፒ ወረዳ ማዕከል፣ የማሻና የጌጫ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት አገልጋዮችና የሰበካ ጉባኤ አባላትን ጨምሮ ሌሎች የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ታድመዋል ።
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …