ማሻ፣ ታህሳስ 17/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ማንቼስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ ይጫወታሉ፡፡
ያለፉትን ተከታታይ ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻሉት ሁለቱም ክለቦች ወደ ድል ለመመለስ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት በኦልድትራፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ኒውካስል ዩናይትድ አራቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ሲይዝ፥ ማንቼስተር ዩናይትድ በአንዱ ድል ቀንቶታል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ በ26 ነጥብ በሊጉ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፥ ኒውካስል ዩናይትድ በ23 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
More Stories
የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷ እንዲሰረዝ መወሰኑ አሳፋሪ ነው፡- የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦጉስቲን ሴንግሆር
ቦርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ