‹‹ሉሲ የእንሰት ኢንተርፕራይዝ ››የእንሰት ውጤቶች ላይ እሴት በመጨመር ለገበያ ለማቅረብ በ2015 ዓ.ም የተቋቋመ ኢንተርፕራይዝ ነው።
ኢንተርፕራይዙ የእናቶችን ጉልበትና ጊዜ የሚቆጥቡ 40 የቆጮ መፋቂያ ማሽኖችን በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚገኙ ማህበራት ማከፋፈሉን የኢንተርፕራይዙ ፕሮዳክሽን ማናጀር ወ/ሪት የትምወርቅ ሠይፉ ይናገራሉ፡፡
ቆጮ በባህላዊ መንገድ እንዲብላላ መሬት ውስጥ ተቀብሮ ከ3-4 ወር ጊዜ መጠበቅ ግድ ይል ነበር፡፡ የኢንተርፕራይዙ አባላት ችግሩን ለመፍታት ያካሄዱት ጥናትና ምርምር ውጤት የሆነው እርሾ ቆጮ ንፅህናውን እንደጠበቀ በ 7 ቀናት ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እንዲብላላለ ማድረግ መቻሉንም ያስረዳሉ፡፡
ቆጮን በባህላዊ መንገድ ለምግብነት ማዋል ብቻ ሳይሆን እሴት ተጨምሮበትና ተቀነባብሮ ዱቄት፣ ኬክ፣ ኩኪስና ዳቦ ሊሆን መቻሉን አብራርተዋል።
የገበያና ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ያሉት ወ/ሪት የትምወርቅ ቆጮን ኬክና ኩኪስ አድርገን ከአገር ውስጥ ገበያ አልፈን ወደ ባህር ማዶ መላክ ጀምረናል ብለዋል።
‹‹እሴት ሰንሰለትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ›› የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰፋፊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የቀረፀው አዲሱ የዘርፉ እሳቤ አንዱ የትኩረት መስክ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት ሚኒስቴር መ/ቤቱ የዕሴት ሰንሰለትን በጥናት በመለየት በየደረጃው ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል መመሪያ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
More Stories
ግብርናን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር የፋይናንስ ብድር አገልግሎት
በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የተቀናጁ የልማት ሥራዎች በክልልና በዞን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ምልከታ ተደረገ
በ10.4 ሚልዮን ብር በጀት ተጨማሪ የገቢ ማመንጫ የሚሆኑ የንግድ ቤቶች ግንባታ በማከናወን ለአገልግሎት እያዋለ መሆኑን በሸካ ዞን የቴፒ አንደኛና መካከለኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አስታወቀ፣