ት/ቤቱ ከዚሁ ግንባታ በየዓመቱ ከ2.7 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ በኪራይ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ት/ቤቶች ደረጃቸውን ለማሻሻልም ሆነ የት/ት ሥራውን ውጤታማ ለማድረግ ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን ሀብት ማመንጨት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እንዲሰሩ መንግስት ይደገፋል።
የቴፒ አንደኛና መካከለኛ 2ተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤትም ከመማር ማስተማር ተግባሩ ባሻገር ለተለያዩ ገቢዎች ማመንጫ የሚሆኑ 24 ክፍል ህንፃዎችን በመገንባት የከተማ ነዋሪውን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።
ያነጋገሪናቸው ተጠቃሚዎች እንደገለፁት ት/ቤቱ ከመማር ማስተማር ባሻገር እንዲህ አይነት ህንፃዎችን በመገንባት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በቅናሽ ዋጋ በማከራየቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለሎችም አርአያ የሆነ ነው ብለዋል።
የትምህርት ቤቱ ምክትል ር/መ ሽመልስ ተስፋዬ እንደገለፀት ትምህርት ቤቱ ከተቋቋመ በርካታ አመታትን ያስቆጠረና በርካታ ምሁራንን ያፈራ እንደመሆኑ አሁን ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የውስጥ ገቢውን እያሳደገ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
በ10.4 ሚልዮን ብር ህንፃው መሰራቱን ገልፀው በዓመት 2.7ሚልዮን ብር ገቢ ት/ቤቱ ከኪራያ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።
ህንፃው በቀድሞ ተማሪዎች፣በአከባቢው ተወላጆችና በመንግስት ድጋፍ የተገነባ መሆኑን ገልፀው በዚህ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን እስከ G+4 እንደሚቀጥል ጠቁመው ገቢው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ማሟያ እንደሚሆን ገልፀዋል።
የቴፒ ከተማ ከንቲባ አማካሪ የሆኑት አቶ አዲሱ ሸዋ በበኩላቸው በከተማው የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ እንዲህ አይነት ተግባራትን የሚያከናውኑ ተቋማትን በማጠናከር እንዲሰራ ከተማ አስተዳደሩ የድርሻውን መወጣቱን ተናግረዋል።
More Stories
ሚኒስቴሩ ለሦስት ኩባንያዎች የማዕድን ምርት ፍቃድ ሰጠ
በክልሉ ከሚገኙ ቡና አቅራቢ ነጋዴዎች ጋር በወቅታዊ የቡና ገበያ ላይ በቦንጋ ከተማ ምክክር እየተደረገ ነዉ
የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያጠናከሩ ተጠየቀ፡፡