“በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” 4ኛ ዙር የተለያዩ ዘርፎች የፐብሊክ ሰርቪስ ግንባር ቀደም የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በክልልና በዞን ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል።
በግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን አንዲሁም የኢንዱስትሪ እምርታ ላይ በአንደኛ ቀን ውሎ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ግብርናን ማዘመንና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ማምጣት ለብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል እና የመንግስት መረጃና የዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ኋላፊ መስፍን ወዳጆ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በመሆኑም ግብርናን በማሻገር የኢንዱስትሪ አብዮትን መቀላቀልና ብልጽግናን እውን ማድረግ ከአባላቱ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
ለዚህም በቴክኖሎጂ ዕውቀት የዳበረ የሚፈጥር፣ የሚፈጥንና የሚዘል አባላት በመሆን አሁን ዓለም የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ መቀላቀል ወሳኝና የሞት ሽረት ጉዳይ ልሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
ብልጽግና በሃሳብ የበላይነት የሚያምን ፓርቲ ነው ያሉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ሰብስቤ ሻዎኖ በበኩላቸው አባላቱ ሃሳብ በማዋጣት እና የጋራ አቋም በመያዝ የመንግሥትን ብሎም የፓርቲ ን ተልዕኮ ማሻገር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ለዚህም የግብርና ዘርፍ እንዲዘምንና ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትራንስፎርም እንዲያደርግ መስራት ከሁላችን ይጠበቃል ብለዋል።
ዓላማው እንዲሳካም የግብርና ቴክኖሎጂ መሬት እንዲወርድና ጾሙን የሚያድር መሬት እንዳይኖር ተግቶ መስራት ከአባላቱ ይጠበቃል ሲሉ አሳስበዋል።
ይህም ለገጠር ትራንስፎርሜሽን በር ከፋች መሆኑን በማመን ለጋራ ለውጥና ለሀገራዊ ብልጽግና መትጋት ጊዜ የሚሰጠው መሆን እንደሌለበትም አቶ ሰብስቤ ገልጸዋል።
የመንግሥትም ሆነ የፓርቲው የልማት ጉዞ ጅማሮ መልካም ነው ያሉት አባላቱ ለውጡ በሁሉም ዘርፎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።
ለለውጡ ስኬት እና ለጋራ ለውጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ግንዛቤ ያገኙበት መድረክ እንደነበርም ዕለቱን አወድሰዋል።
More Stories
በቀጣዮቹ ቀናት በበርካታ አካባቢዎች የክረምቱ ዝናብ ተጠናክሮ ይቀጥላል
በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ እንዲፈጠር የምግብ -ስርዓትና ስርዓተ – ምግብ ትግበራዎችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ
267ኛው የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ መመረጡን አስመልክቶ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡ ምዕመናን ደስታቸውን ሲገልፁ