ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ነው።
ኢንስቲትዩቱ በበጋው የአየር ሁኔታ በሚኖር ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በትግራይ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ብሏል፡፡
ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት አከባቢዎች የዝናብ መቆራረጥ ሊኖር እንደሚችልም ተጠቁሟል።
ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንደ ቦረናና ጉጂ ዞኖች፣ ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛ ዝናብ የሚኖራቸው መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል።
የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል ደግሞ ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል የምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙም ተነግሯል።
ኢንስቲትዩቱ ግንቦት ላይ የሰጠው የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ትንበያ መሬት ላይ ከተከሰተው ጋር የተጣጣመ እንደነበረም ተነግሯል፡፡
ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ እንዲሰብሰቡ ማድረግ ከመደበኛ በታች ዝናብ በሚስተዋልባቸው የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል የሚገኘውን የዝናብ መጠንና ስርጭት በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ሲል ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል ሲል የዘገበው ሸገር ኤፍ ኤም ነው።
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።