September 15, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።

ማሻ ፣ የሀምሌ 04፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የሸካ ዞን ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የ2017 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለኢትዮጵያ ከፍታ አራት” በሚል መሪ ቃል ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በማሻ ከተማ ተካሂዷል ።

በማስጀመሪያው መረሃ ግብር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት

የሸካ ዞን ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 60 ሺህ በጎ ፍቃደኞችን በማሳተፍ 216 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቋሚ በማድረግ 60 ሚልዮን ሀብት ለማዳን መታቀዱን አስታውቀዋል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሰው ተኮር ስራዎች በርካታ ተግባራት በመከናወኑ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገቡን ገልፀዋል ።

በዘንድሮም የክረምት መረሃ ግብር የአቅሜ ደካሞች ቤት ማደስ፣ ማዕድ ማጋራት፣ የወባ ስርጭትን መከላከልና የትራፍክ ደህንነት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደምከናውኑ ጠቁመው የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የሸካ ዞን የመንግሰት ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ የሀገር በቀል ዕሰቶችን ለማጎልበት የበጎ አድራጎት ስራ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም በባለቤትነት ስሜት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የቀረበው ዕቅድ ከአፈፃፀሙ ጋር ስነፃፀር ውስን መሆን፣ ተግባራትን ለቅሞ ሪፖርት የማድረግና ከልየታ አንፃር ያለው ውስንነት በቀጣይ መስተካከል እንዳለባቸው ጠይቀዋል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞን ፣ የዞኑ የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ ጨምሮየየመዋቅሮቹ አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ በዛብህ ታደሰ