ማሻ ፣ የሀምሌ 02፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የትራንፎርመሽን ዕቅድ የእስካሁን አፈጻጸምና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይቱ የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ እንደተናገሩት፤ እንደሀገር የፍትህ እና የዳኝነት ሥርዓቶችን በማሳለጥ ለህዝቡ ተደራሽነቱና ፍትሃዊነት የተረጋገጠ አገልግሎት ለመስጠት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።
የፍትህና የዳኝነት ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ማሳለጥ የሚያስችል የፍትህ ተቋማት ዘርፍ ትራንፎርመሽን ወደ ትግበራ ገብተው ውጤቶች እየተመዘገቡ ናቸውም ብለዋል ሚኒስተሯ።
ለውጤታማ ፍትህ ትራንስፎርመሽን ሥራዎች በፌደራልና በክልል ተቋማዊ ቅንጅት በማጠናከር በመደጋገፍ እና በመቀናጀት ሥራዎች እንደሚሰሩ ነዉ ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ የገለጹት።
ማህበረሰብ ተኮር ፍትህ መሠረት ላደረጉ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና በመስጠትና በማጠናከር ባህላዊ ፍርድ ቤቶች አሰራሩን ተከትለው ለማህበረሰቡ ትክክለኛ እና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።
በቴክኖሎጅ የተደገፈ የወንጀል ምርመራና የክስ ሥርዓት ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ በመሆኑ ይህንን ማጠናቀቅና በተሟላ ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል።
በክልሉ የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የትራስፎርመሽን ሥራዎች የተሻለ አፈጻጸም የታዬ በመሆኑ ይህውም የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የጀመረውን የድጋፍ ሥራዎችን እንደሚያጠናክርም ክብርት ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ ጠቅሰዋል።
በክልሉ የዘርፉ ተገልጋይ ተኮር እርካታ ከፍ እንዲል ተቋማዊ አደረጃጀት ማጠናከር ፣የማህበረሰቡ ጥያቄ አዳምጦ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ትኩረት እንዲሰጥም አሳስበዉ ተቋሙን በግብዓትና በሰው ኃይል ማደራጀት እና የዘርፉ ባለሙያዎች ጥቅማጥቅምና መሠል ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከክልሎች ጋር በቅንጅት ይሰራልም ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤በክልሉ የፍትህ እና የዳኝነት ሥርዓቶችን ማሳለጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
የፍትህ ዘርፍ ተቋማት ትራንፎርመሽን ዕቅድ እንዲሳለጥ የህግ ማሻሻያዎችን ማውጣት፣ተግባሩን የሚመራ ግብረሃይል ማቋቋምና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ምክክሮች እየተደረጉ እንደሚገኙ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት።
ለፍትህ እና ዳኝነት ሥርዓቶች መሳለጥ ተቋማዊ አቅም መገንባት በተለይም የተቋሙን የመረጃ ጥራት እንዲረጋገጥ ሥራዎችን በቴክኖሎጅ ማዘመን ፣ለባህላዊ ፍርድቤቶች እውቅና መስጠትና የማጠናከር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ነዉ ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ የጠቀሱት።
በክልሉ ከፍትህና ዳኝነት ሥርዓት በተያያዘ ከህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ የመመለስ ሥራዎች ይጠናከራሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የዘርፉ ባለሙያዎች አቅም ግንባታ እና የዘርፉ ባለሙያዎች ለሚያነሱት ጥያቄዎች አስፈላጊ ምላሽ እንዲሰጥ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
በክልሉ የህዝቡን ፍላጎት በመፈተሽ የፍትህ እና የዳንኘት ሥርዓትቶችን ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሁሉዓቀፍ ተግባራት እንደሚናከረም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ እሸቱ ጎደቱ ተናግረዋል።
ክልል ኮሚኒኬሽን
More Stories
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና በሚዛን-ቴፒና ቦንጋ የዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝደንቶች፣ ምክትል ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ተጀምሯል።