ማሻ ፣ የሰኔ 25፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ኢትዮጵያ እየተጠናቀቀ ባለው የበጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፌዴራልና ከክልሎች የፀጥታ፣ ከግብርናና ንግድ ዘርፎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ የቡና ምርትን ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ በመሆኑ ውጤት ተገኝቷል።
በተጨማሪም ወደ ውጭ የሚላከውን የቡና ጥራት ይበልጥ ለማስጠበቅ ተጨማሪ አራት የቅምሻ ማዕከላት ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም የቡና ምርት በጥራትም ሆነ በብዛት በተሻለ ደረጃ ማደጉን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የተገኘውን ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሕገ-ወጥ የቡና ንግድና ዝውውር መግታት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘግቧል።
ባለፉት 11 ወራት 409 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ መቅረቡ የሚታወስ ነው።
ኢቢሲ
More Stories
ሚኒስቴሩ ለሦስት ኩባንያዎች የማዕድን ምርት ፍቃድ ሰጠ
በክልሉ ከሚገኙ ቡና አቅራቢ ነጋዴዎች ጋር በወቅታዊ የቡና ገበያ ላይ በቦንጋ ከተማ ምክክር እየተደረገ ነዉ
የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያጠናከሩ ተጠየቀ፡፡