ክልላዊ የበጀት ድልድሉ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ መደረግ አለበት። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ማሻ ፣ የሰኔ 23፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ክልላዊ የበጀት ድልድልና የገቢ እቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር በቦንጋ ከተማ እየካሄደ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ከዚህ ቀደም ሲተገበር የነበረው ክልላዊ የበጀት ቀመርና ድልድል ለክልል ማዕከል የካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ አነስተኛ ሚና የነበረው በመሆኑ በቀጣይ ይህንን አሰራር በማሻሻል የ2018 በጀት ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በበጀት አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ ካለፈው ዓመታት የታየውን ልምድ በመቀመር ውጤታማ የበጀት አስተዳደርና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የጠቆሙት።
መደበኛ የመንግሥት የግዴታ ወጪዎችን ለመሸፈንና ክልላዊ ልማት ለማሳለጥ ክልላዊ የገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ የገብ እቅድ በማሳደግ በተሻለ መልኩ መሰብሰብ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በበኩላቸው፥ የ2018 የክልሉ በጀት ዋና ዋና ተግባራት ይሳካ ዘንድ የታቀዱትን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ስትራቴጂና ፖሊሲ ለማስፈፀም በሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በዋናነት ሰብዓዊ አገልግሎቶች ፣ አስገዳጅ የመንግስት ወጪዎች ፣ለተፈጥሮና ድንገተኛ አደጋዎች የሚሆኑ መጠባበቂያ ወጪዎች ላይ ቅድሚያ በመስጠት ተግባራዊ እንደሚሆን የገለጹት ኃላፊዎ
ተጀምሮ ዕድሜ ያስቆጠሩትን የልማት ፕሮጀክቶችን እንዲሁ ቅድሚያ በመስጠት የሚፈፀምበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ የ2018 በጀት ዓመት የክልሉ የገቢ እቅድ በዝርዝር ያቀርቡት ሲሆን በቀረበው የገቢ እቅድ ላይም ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ የባለ በጀት መስሪያ ቤህ የስራ ኃላፊዎችና የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
ክልል ኮሚኒኬሽን
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።