ማሻ ፣ የሰኔ 23፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ የዜና ጣብያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነውን ቲክ ቶክ የሚገዙ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን አስታዉቀዋል።
የገዢዎቹን ማንነት ከሁለት ሳምንት በኋላ ይፋ እንደሚያደርጉም ነው ፕሬዝዳንቱ የገለፁት።
ንግግሩ አሁን ላይ እየተደረገ መሆኑንና ከቻይና ፈቃድ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ያደረጉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
ባለፈው ዓመት ባይትዳንስ የተሰኘው የቻይናው ኩባንያ የቲክቶክ መተግበሪያን ለአሜሪካዊ ባለሃብት የማይሸጥ ከሆነ እንዲዘጋ መወሰኑ ይታወሳል።
ሆኖም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስልጣን በመጡ ጊዜ ሊዘጋ የነበረውን ቲክ ቶክን በ3 ወር አራዝመው ለአሜሪካዊ ድርጅት እንዲሸጥ ጥሪ አቅርበው ነበር።
አሁን ላይ ገዢ እንደተገኘ እና ንግግር ላይ መሆናቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት የገዢዎቹን ማንነት በይፈ እንደሚያስታውቁ ጠቅሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቅርቡ ቲክቶክ ለተጨማሪ 90 ቀናት በሀገረ አሜሪካ እንዲሰራ መፍቀዳቸዉ የሚታወስ ነዉ።
ኢቢሲ
More Stories
የአውሮፓ ህብረት ያወጣቸውን ደንቦች መሠረት በማድረግ የግብርና ምርቶች ከደን ጭፍጨፋ ነፃ ሆነው እንዲመረቱ ከማድረግ አንፃር የግብርና ባለሙያዎች ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ ።
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ