June 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሕንድ የአውሮፕን መከስከስ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት …

ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‎‎ ዶክተር ፕራቲክ ጆሺ ኑሮን ለማሸነፍ ከባለቤቱ እና ሶስት ልጆቹ ተለይቶ ለስድስት ዓመታት ኑሮውን በእንግሊዝ ለንደን አድርጎ ነበር፡፡

በጊዜ ሒደት ውድ ባለቤቱን እና ልጁቹን ወደ ለንደን አምጥቶ ደስተኛ ሕይወት የመኖር ሕልምን ሰንቆ ብዙ ችግሮችን አሳልፏል፡፡

ከዓመታት ውጣ ውረድ በኋላም አስፈላጊውን ሁሉ በማሟላት ቤተሰቦቹን ወደ ለንደን የመውሰዱ እቅድ እውን ሆነ፡፡

ባለቤቱ፣ ሁለት መንታ ልጆችና አንድ ሴት ልጁም በለንደን የተሻለ ሕይወት ለመኖር ሒደቱ ማለቁን ሲሰሙ ተደሰቱ፤ ለጉዞም መሰናዳት ጀመሩ፡፡

በምትኖርበት አካባቢ እውቅ የሕክምና ባለሙያ የሆነችው ባለቤቱ ዶክተር ኮሚ ቪያስ ከጉዞ ሁለት ቀናት በፊት ሥራዋን በፈቃደኝነት ለቀቀች፡፡

ከዚያም ቤተሰቡ ወደ ለንደን ለመብረር ሻንጣውን ሸከፈ፡፡ በለንደን በአዲስ መንፈስ አዲስ ሕይወት ለመጀመር በማለምም ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ተሰናበቱ፡፡

የአንድ ቤሰተብ አባላቱ ለዓመታት የጠበቁት ቀን ደርሶም በጉጉትና በተስፋ ወደ ለንደን ለመብረር በአሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተዋል፡፡

የበረራ ቁጥሩ 171 በሆነው አውሮፕላን ከገቡ በኋላም በረራ ከመጀመራቸው በፊት ከታች የተቀመጠውን በራሳቸው የተነሳ ፎቶ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው አጋሩ፤ ወዳጅ መዘዶቻቸውም መልካሙን ሁሉ ተመኙሏቸው፡፡

ይሁን እንጂ የተሳፈሩበት አውሮፕላን በረራ በጀመረ 30 ሰከንዶች ውስጥ በአሰቀቂ ሁኔታ ተከሰከሰ፤ ዶ/ር ፕራቲክ ጆሺ፣ ባለቤቱ፣ ሁለት መንታ ወንድ እና አንዲት ሴት ልጆቹ በአደጋው ሕይወታቸው አለፈ፡፡

የዶ/ር ፕራቲክ ጆሺ እና ቤተሰቦቹ በለንደን አብሮ የመኖር ሕልምም በአሳዛኝ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ሆነ፡፡

ከምዕራብ ሕንድ አሕመዳባድ አውሮፕላን ማረፊያ 242 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረ የሕንድ አውሮፕላን ትናንት የመከስከስ አደጋ ያጋጠመው መሆኑ ይታወቃል።

ፋና