ማሻ ፣ የሰኔ 04፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ቡና ዕሰት ሰንሰለት ዙርያ ያካሄደዉን የጥናት ዉጤት በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት እያካሄደ ነዉ።
ጥናቱ በክልሉ ባሉት ሶስት ቡና አምራች ዞኖች ላይ የተካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል።
በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይረክተር አቶ አስራት መኩሪያ ቡናን ከምርት ጀምሮ እስከ ተጠቃሚ ድረስ ያለዉን ሰንሰለት ምን እንደሚመስል የተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ የቡና እሴት ሰንሰለት የተደረገዉ ይህ ጥናት ዉጤት በክልሉ ሶስት ቡና አምራች ዞኖች ላይ የተካሄደ መሆኑ ተጠቁመዉ የተጠኑ የጥናት ዉጤቶች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ከዘርፉ የምገኘዉን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የቡና ጥራትና ግብይትን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘዉን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአምራች አርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የቡና ግብይት ሰንሰለት በዓለም አቀፍ ደረጃና በሀገራችን ምን እንደሚመስል በመገምገም ለቀጣይ የተሻለ ስራ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ።
የቡና ሰንሰለት ላይ ባለስልጣኑ ያስጠናዉን የጥናት ዉጤት በዶክተር ሀብታሙ ገ/ስላሴ በኩል እየቀረበ ይገኛል።
በቸርነት አባተ
More Stories
ቴፒ የምርት ጥራት ምርመራና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገለፀ።
ከቡና ወጪ ንግድ ከ2 ነጥብ 24 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የቡና ምርት አግኝታለች