ማሻ ፣ የሰኔ 03፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትን ለማምጣት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፉ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ዛሬ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂደናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መረጃ ገልጸዋል።
በውይይታችን በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የገቡ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና በሁለተኛው ዙር ለመግባት ዝግጅት ያጠናቀቁ ተቋማትን ቅድመ ዝግጅትን ተመልክተናል ነው ያሉት፡፡
በተጨማሪም የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መሶብን ለማስጀመር እያከናወኑ የሚገኙትን የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴ ሪፖርትን ገምግመናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመጀመሪያ ዙር ወደ መሶብ የገቡ ተቋማት በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ታይቷል ብለዋል።
በሁለተኛ ዙር ወደ መሶብ የሚገቡ ተቋማት እና በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚከናወኑ ተግባራት እንዴት መስራት እንዳለባቸዉ እና ለተግባራዊ እንቅስቃሴያቸው አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።
ፋና
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።