ማሻ ፣ የግንቦት 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ምሽት በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነሥርዓት የኢትዮጵያን ታላቁን የክብር ኒሻን ለቢል ጌትስ ሸልመዋል።
ይኽ የከበረ ሽልማት የጌትስ ፋውንዴሽን ባለፉት 25 አመታት በኢትዮጵያ ላበረከታቸው አሻጋሪ ሥራዎች እና ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ በጎ ተፅዕኖዎችን ያከበረ ነዉ ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ለቢል ጌትስ ፋውንዴሽን የ25 አመታት አሸጋጋሪ ሥራዎች ምስጋና አቅርበዋል።
ቢል ጌትስ ከቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅነት ወደ በጎ አድራጊነት ያደረጉትን ጉዞ በማውሳትም ዝቅ ብሎ በማገልገል፣ በአክብሮት እና በእኩልነት እምነት ላይ የተመሠረተውን አገልግሎታቸውን አድንቀዋል።
ፋውንዴሽኑ በጤና፣ ግብርና፣ ዲጂታል መታወቂያ የሚያደርገው ጥረት ብሎም ጠንካራው በመከባበር ላይ የተመሠረተ ትብብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ተወስቷል።
Fana
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …