June 5, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በ9 ነጥብ 3 ሚለየን ብር የተገዛው የሞተር ሳይክልና የታብሌት ሞባይል ለዞኖች ድጋፍ ተደረገ

በ9 ነጥብ 3 ሚለየን ብር የተገዛው የሞተር ሳይክልና የታብሌት ሞባይል ለዞኖች ድጋፍ ተደረገ

ማሻ ፣ የግንቦት 25፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)በክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በጀት ድጋፍ የፕሮግራሙ ስራ ለማሳለጥ የተገዛው 43 ሞተር ሳይክሎችና 15 የታብሌት ሞባይሎች በፕሮግራሙ ለሚደገፉ 15 ወረዳዎች ፣ለዞኖችና ለክልሉ የፕሮግራሙ ፈጻሚ መ/ቤቶች እንደሆነ በክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወንድወሰን ሁሰን ገልጸዋል።

የፕሮግራሙ ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት ፕሮግራሙ በክልሉ ከሚሰሩት ተግባራት አንዱ የአቅም ግንባታ ዘርፍ በመሆኑ ስራውን በአግባቡ ለማሳለጥ አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አንስተዋል ።

በመሆኑም ለዞኖች 6፣ ለ15 ወረዳዎች 30 ሞተር ሳይክልና 15 ታብሌት ሞባይል እንዲሁም ለክልል ፈጻሚ መ/ቤቶች 7 በአጠቃላይ 43 ሞተር ሳይክሎች ከ9 ነጥብ 3 ሚለየን ብር የተገዙ መሆናቸዉን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል ።

በመሆኑም ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ ዓላማ እንዲሁም ለክትትልና ድጋፍ ስራ እንዲውል በወረዳው ላለው አስተባባሪና ለክትትል ስራ ለተቀጠሩ መሃንዲሶች የቀረበ በመሆኑ በጥንቃቄ እንዲያሽከረከሩ አቶ ወንድወሰን አሳስበዋል ።

ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የመጡ ሞተሩንና ታብሌት ሞባይሉ ተረካቢዎች ተግባሩን ውጤታ ለማድረግ ፕሮግራሙ ይህን ግብዓት በማቅረቡ ምስጋና አቀርበዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም በታችኛው መዋቅር በቂ ተሽከሪካሪና ቴክኖሎጂ ባለመኖሩ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ መቸገራቸውን በመግለጽ አሁን ጊዜንና ጉልበትን ለመቆጠብ፣ ድጋፍና ክትትሉን ለማጠናከርና እንዲሁም በፕሮግራሙ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል ።

ክልል ኮሚኒኬሽን