ማሻ ፣ የግንቦት 18፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) “የዘመነ የፈተና አስተዳደር ሥርዓት ለትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም ሀገራዊና ክልላዊ የፈተና አስተዳደር የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተኳሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማዉ ዘዉዴ በትምህርት ሰክተር ዘርፍ በተሰሩት ስራዎች የትምህርት ምዘና እና የፈተና አስተዳደር ስረዓት ላይ ለዉጥ መመዝገቡን ገልፀዋል።
በዘንድሮ ዓመት በክልሉ ባሉ አራት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለ19ሺህ127 ተማሪዎች የሀገራዊ መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ገልፀዉ ከእዚህም ዉስጥ 2ሺህ690 ተማሪዎች በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
የትምህርት ስልጠና ስረዓት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ በክልሉ የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል እንደሚሰጥ ጠቁመው በክልሉ ለመጀመሪያ ግዜ ወጥ በሆነ ስታንዳርድ በሚሰጠው ፈተና 38ሺህ 593 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ገልፀዋል።
የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠር አቶ ነጋ አበራ በበኩላቸዉ በዘንድሮ አመት የሚሰጡ ክልላዊና ሀገራዊ ፈተና ስከታማ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዉ በዚህ ረገድ የፈተና አስተዳደርን በበላይነት የሚመሩ አካላት በጋራ ኃላፍነታቸዉን መወጣት አለባቸዉ ብለዋል ።
ለክልላዊና ሀገራዊ ፈተና ግብአትን በአግባቡ በማማላትና ስምሪት በመስጠት እንድሁም በህደቱ ልፈጠሩ የሚችሉ ችግሮች የእርምት እርምጃ በመዉሰድ የፈተና አስተዳደር ስራን ዉጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።
የዝግጅት ምዕራፍ የተሰሩ ስራዎች ዙርያ የዉይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየት የሰጡ ስሆን በተለይም የኩረጃ ባህልን ለማስቀረት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዉ በፈተናዉ ወቅት ልከሰቱ የሚችሉ የነት ወርክ መቆራረጥ ፤ የነዳጅ ፍጆታና መሰል ጉዳዮችን አንስተዉ ዉይይት ተደርጓል።
በመድረኩ የክልሉ አስተባባሪ አካላትና ሌሎች የቢሮ ኃላፊዎች፣የዩኒቨርሲቲ አመራሮች እንዲሁም የክልልና የዞን የዘርፉ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በቸርነት አባተ
More Stories
የአየር ጠባይ ትንበያ መረጃ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት በታቀደው መሠረት እንዲከናወን ድርሻውን ተውጥቷል – ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር)
መጪው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ተጽዕኖ ሊያደርስ ይችላል ተባለ።
የወባ መከላከያ ክትባት በሽታውን ለማጥፋት በማለም ለተጀመረው ርብርብ ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ።