የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለፁት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የልጅነት ልምሻ በሽታ መከላከያ ክትባት በክልላችን ዉጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግት ስራዎች ሲሰሩ እንደቆዩና በዘመቻዉም 564 ሺህ 624 እድሚያቸዉ ከ5አመት በታች የሚሆኑ ልጆች ተደራሽ እንደሚደረጉ ገልጸዋል::
የቢሮ ኃላፊ እንደገለጸት በ1ኛዉ ዙር ዘመቻ ከታቀደዉ እቅድ 100% በላይ ክትባቱን ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በ2ኛዉ ዙርም 1ኛ ዙር የወሰዱ ልጆች ተደረሽ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዉ ሁሉንም ታላሚዎች ተደራሸ ለማድረግ በየደረጃዉ የሚገኙትን ባለድርሻ አካላት ባሰተፈ መልኩ ዘመቻዉ መመራት እንዳለበት አሳስበዋል::
የቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጸት በዘመቻዉ ወቅት ተቀናጅተዉ የሚሰሩ ተግባራት ኤም ፖክስ (M_Pox) በሽታ ግንዛቤ የመፍጠር እና የአሰሳ ስራ፥ በኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ወቅት የተለዩ የተወሳሰበ የስርዓተ ምግብ ችግር ያለባቸዉን ልጆች ወደ ጤና ተቋም ሄደዉ ህክምና እንዲጀምሩ አሳስበዋል።
እድሜያቸው ከ1አመት በላይ ሆነዉ ክትባት ያልጀመሩና ጀምረዉ ያቋረጡ ልጆች ክትባት እንዲጀምሩ ማድረግ፤ቆልማማ እግር ችግር ያለባቸዉን ልጆች ልየታ፤የፊስቱላ ልየታ ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን በዘመቻዉ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተግባራትን በትኩረት እንዲተገብሩና እንዲመሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በመቀጠልም ዘመቻዉን በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የተለመደዉን ትብብር እንዲያደርጉ የቢሮ ኃላፊ አሳስበዋል::
More Stories
ሕፃናት ወደ አፋቸው የሚያስገቧቸው ባዕድ ነገሮች እስከ ሞት ለሚያደርስ አደጋ እያጋለጣቸው ነው፦ የሕፃናት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት
የክልሉ ጤና ባለሙያዎችና የጤና ተቋማት አመራሮች ያሳዩት አቋም ለህዝባቸው ያላቸውን ውግንና እና ለሙያቸው ያላቸውን ክብር ያረጋገጡበት ነው :- የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለፁ ።
ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ