May 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የ2018 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች የበጀት ዕቅድ እየተገመገመ ነዉ።

ማሻ ፣ የግንቦት 16፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች ዕቅድ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት እየተገመገመ ይገኛል።

በግምገማ መድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ያለዉን ዉስን በጀት በካፒታል ፕሮጀክቶች ላይ በፍትሃዊነት፣በአዋጭነትና ከአስፈላጊነት አኳያ አይቶ በጀት መመደብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ከዚህ አኳያ ያለዉን ዉስን ሃብት አስቀድሞ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለመጨረስ እንዲሁም ዉጤታማ ስራ ለመስራት የካፒታል ፕሮጀክቶችን የበጀት ፍላጎት መገምገም እንዳስፈለገ ጠቅሰዋል።

ነባር የካፒታል ፕሮጀክቶች እና አዳዲስ የካፒታል ፕሮጀክት በጀት ጥያቄ ያላቸዉ ቢሮዎች ዕቅዳቸዉን እያቀረቡ ይገኛሉ።

ክልል ኮሚኒኬሽን