May 28, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በህዝቦች መካከል ያለዉን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከርና ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የየአካባቢዉን ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ በዘላቂነት ማስቀጠል እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።

ሻ ፣ የግንቦት 17፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) 2ኛ ዙር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰላምና የልማት የትብብር ፎረም በሚዛን አማን ከተማ እተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የቆየና የጠበቀ ትስስርና በርካታ መልካም እሴቶች እንዳለ አዉስተዋል ።

በሌላ በኩል በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በሆኑ አንዳንድ አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚከሰቱት ግጭቶችን በክልሉ ህዝቦች ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ የመፍታቱ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም በዘላቂነት ትኩረት ሰጥቶ አንዲሰራ አሳስዋል።

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለምቱ ኡሙድ በበኩላቸዉ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሁለቱ ክልል ህዝቦች ከዚህ ቀደም በፍቅርና በመተሳሰብ የሚኖሩ መሆናቸዉን አስታዉሰዉ በቀጣይ ለጋራ ሰላምና የልማት ተጠቃሚነት ሁሉም የሚጠበቅበትን እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የሰላምና የልማት የትብብር ፎረሙ ላይ የተገኙት የኢፈዲሪ ሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ መሐመድ እንድሪስ በበኩላቸው ክልሎቹ በተፈጥሮ ጸጋ የበለጸጉ ከመሆናቸዉም በተጨማሪ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሰርቶ የሚለወጥበት መሆኑን ተናግረዋል።

ሆኖም ህዝቡን የማይመጥኑ ግጭቶች አልፎ አልፎ ስለሚስተዋሉ በክልሉ ህዝቦች ዉብ የግጭት አፈታት ዜዴ ግጭቶችን መፍታትና መከላከል ላይ ቀጣይነት ባለዉ መልኩ በትኩረት እንዲሠራ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የሁለቱ ክልል ህዝቦችን ሰላምናና ልማት በቀጣይነት ልያጠናክሩ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ በመሚከር የጋራ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ይጠበቃል።

በመድረኩ የፈደራልና የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል ።

ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ