May 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከውሃ ሀብት የሚገኘውን ጥቅም ለማጎልበት መስራት ያስፈልጋል – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)

ማሻ ፣ የግንቦት 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ሀገሪቱ ያላት የዉሃ ሀብት ከኢትዮጵያ አልፎ ለአጎራባች ሀገራት ተደራሽ እየሆነ መምጣቱን የዉሃና ኢንጂነር ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ተናገሩ።

በዉሃና ሀይድሮ ዲፕሎማሲ ላይ ትኩረት ያደረገ ምክክር በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

ሚኒስትሩ በዚህን ወቅት እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከ1 መቶ 20 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር በላይ የዉሃ ሀብት ቢኖራትም ባላት ሀብት ልክ እየተጠቀመች አይደለም።

በመሆኑም ቀጥሎ ባሉት ጊዜያቶች ያሉትን የዉሃ ሀብቶች በሚገባ በመጠቀም የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ለዚህም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በምክክሩ የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ፋና