ማሻ ፣ የግንቦት 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ለዚህም የሚሆን ቅድሜ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ደስታ ገነሜ እንደገለፁት በዘንድሮ ዓመት በሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎችን ዉጤታማ ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አምና በነበረዉ የአገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በክልሉ ሰፊ ቁጥር ያላቸዉ ትምህርት ቤቶች አንድም ተማር ወደ ዩንቨርሲቲ ያላስገቡ ትምህርቶች መኖራቸዉን ያስታወሱት ዶክተር ደስታ በዘንድሮ አመት ችግሩ ጎልቶ እንዳይታይና ትምህርት ቤቶቹ ዉጤታማ እንዲሆኑ የተለያዩ ኢንሼቲቭቦች ተቀርጾ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ ያሉትን የትምህርት ይዘት መሸፈንን ጨምሮ የልዩ ማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራምን በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየተደረገ ነዉ ብለዋል።
በክልሉ በዘንድሮ አመት በሚሰጠዉ የ12ተኛ ክፍል የአገር አቀፍ ፈተና አጠቃላይ 19ሺህ 127 ተማሪዎች ፈተናዉን እንደሚፈተኑ የገለጹት ዶክተር ደስታ ከእነዚህ ተማሪዎች ዉስጥ 2ሸህ 690 ተማሪዎች የኦንላይን ፈተና እንደሚፈተኑ ገልፀዋል።
የኦንላይን ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችም በክልሉ ዉስጥ ባሉ አራት ከተማ አስተዳሮች ዉስጥ ባሉት አስራ አንድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎች በስነ -ልቦና ዝግጁ መሆን እንዳለባቸዉ የጠቆሙት ዶክተር ደስታ ወላጆችም የድርሻቸዉን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ቸርነት አባተ
More Stories
ከውሃ ሀብት የሚገኘውን ጥቅም ለማጎልበት መስራት ያስፈልጋል – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች
አቶ አንዱአለም ጌታቸው የማሻ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ፡፡