ማሻ ፣ የግንቦት 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በአንድ ሳምንት ውስጥ ለ11 ሚሊየን ህፃናት የኩፍኝ ክትባት መሰጠቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በሀገር አቀፍ ደረጃ ኩፍኝን ጨምሮ በየጊዜው የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚያስችል የተቀናጀ የክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።
በጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ የህፃናት እና አፍላ ወጣቶች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ማሪያማዊት አስፋው በተጀመረው የክትባት ዘመቻ ጥሩ ውጤት እየታየበት መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሸን ገልጸዋል።
የቫይታሚን ኤን ጨምሮ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ህፃናትን መለየት፣ ከተወለዱ ጀምሮ ምንም ክትባት ያልወሰዱ ህፃናትን እንዲሁም በወሊድ ምክንያት የተጎዱ እናቶችን መለየት፣ የክትባት ክትትል ባለማድረግ ለህመም የተጋለጡ ህፃናትን የመለየት ስራ በዘመቻው እየተከወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የክትባት ዘመቻው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሶማሌ ክልል ውጭ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ መሆኑን አንስተው÷ ባለፈው አንድ ሳምንት ለ11 ሚሊየን ህፃናት የኩፍኝ ክትባት ተደራሽ መሆኑን አመላክተዋል።
በአዲስ አበባ እና በሶማሌ ክልልም የክትባት ዘመቻው በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸው÷ ለአስር ቀናት በሚዘልቀው የክትባት ዘመቻ ከ9 ወር እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ 17 ነጥብ 5 ሚሊየን ህፃናት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ፋና
More Stories
መንግስት የጤና ባለሙያዎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንካራ ስራዎችን እየሰራ ነው – ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ
የማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት መጀመር በአቅራቢያችን ህክምና እንድናገኝ አስችሎናል-ነዋሪዎች
በዞኑ ከ48 ሺህ 3መቶ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ገለፀ።