ማሻ ፣ የግንቦት 13፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የሸካ ዞን ማሻ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በማሻ ከተማ አካሂዷል ፡፡
የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ አሰለፈች ገዘሀኝ ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን ተናግረዋል ።
አፈ ጉባኤዋ አክለውም የምክር ቤቱ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች ስኖሩ በአሰራሩ መሠረት አስቸኳይ ጉባኤ መደረጉን ገልፀዋል ።
ምክር ቤቱ በውሎው የማሻ ከተማ ም/ቤት 2ኛ ዙር 12ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ እና የቀረበ ሹመትን መርምሮ ማጽደቅን የተመለከተ ስሆን የማሻ ከተማ ም/ቤት 2ኛ ዙር 12ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የቀድሞው ከንቲባ ከሀላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በሸካ ዞን የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ አቅራቢነት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ በምትካቸው አቶ አንዱአለም ጌታቸውን የከተማው ከንቲባ በማድረግ ሹሟል፡፡
አድሱ ከንቲባም በተለያዩ የመንግስት ስራ ሀላፊነቶች ላይ ስሰሩ መቆየታቸውን ማህደራቸው ያመላክታል ።
ከንቲባውም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ በመፈፀም አስቸኳይ ጉባኤው ተጠናቋል ።
ዘጋቢ፡- በዛብህ ታደሴ
More Stories
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች
ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ያለማቋረጥ በመተግበር ምሳሌ ሆናለች – ገመዶ ዳሌ (ዶ/ር)
በተገባደደዉ የበልግ አዝመራ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የእንሰት ችግኝ መትከሉን የአንድራቻ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።