ማሻ ፣ የግንቦት 12፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በኢትዮጵያ አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች ምቹ አጋጣሚ እየፈጠረ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታዬ በድሬዳዋ ከተማ የተገነባውን የፓዮኔር ሲሚንቶ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማስፋፊያ ፕሮጀክት መርቀዋል።
በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ እና በቻይና ባለሃብቶች አጋርነት የተገነባው ፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው።
የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፍ አልሚ ባለሃብቶች አጋርነት የዕውቀት ሽግግርና የካፒታል ፍሰትን እንዲሁም ምርታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም የኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት ጥልፍልፍ መንገዶችን ይጠይቅ እንደነበርም አውስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች ምቹ አጋጣሚ እየፈጠረ እንደሚገኝም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢቢሲ
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …