ማሻ ፣ የግንቦት 11፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በክልሉ በማዕድን ልማት የተሰማሩ ማህበራትና ድርጅቶች የአካባቢ ጥበቃና የማህበራዊ ደህንነት ህግ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር አድርገዋል።
የማዕድን ልማት የአካባቢ ጥበቃና የማህበራዊ ደህንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሃብቶችን በማልማት ለሀገር ጥቅም በጋራ መስራት ይገባል ተብሏል።
በኢትዮጵያ የአከባቢ ብክለትን በመከላከል ለሰዉ ልጆች ሚቹ አኗኗር ሁኔታ ለመፍጠር መንግስት ዘርፌ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ደን አከባቢና አየር ንብረት ለዉጥ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የአየር ንብረት ለዉጥ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደሙሴ ደንቦ ባቀረቡት ሰነድ ገልፀዋል ።
አከባቢ ጥበቃ በሚመለከት የህግ ክፍተት ያለመኖሩን የጠቆሙት የክልሉ ደን አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አስራት ገ/ማርያም የወጡ ህጎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ዉስንነቶች መኖራቸዉን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ከመግባታቸዉ በፊት የአከባቢ ተዕጽኖ ግምገማ በማካሄድ መሆን እንዳለበት የጠቆሙት ዶክተር አስራት የማዕድን ዘርፍ ፍቃድ አሰጣጥ ህደት የአከባቢና ማህበረተሰብ ተፅዕኖ ግምገማን መሰረት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በማዕድን ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች ተፈጥሮ ላይ ችግር ሳያስከትሉ ያለዉን ሀብት መጠቀም እንዳለባቸዉ ጠቁመዉ መንግስትም የራሱን ሚና እንደሚወጣ ገልፀዋል።
የአየር ንብረት ለዉጥ ድንበር የለሽ በመሆኑ ሁሉም አካላት ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ያስገነዘቡት የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርግስ ናቸዉ።
በቸርነት አባተ
More Stories
የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አመርቂ ስኬት አስመዝግቧል – ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ
ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ተፈረሙ
ወደ ሀገር ውስጥ የተጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ደረሰ