ማሻ ፣ የግንቦት 11፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት በሚል መሪ ቃል ከቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎችና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር በቴፒ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳብ አቶ አበበ ማሞ እንደገለፁት እንደ ሀገር መከላከልንና አክሞ ማዳን መሠረት ያደረጉ የጤና ፓሊስዎችን በመከተል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ውጤት እየተመዘገበ እንደምገኝ ገልፀዋል ።
ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ፣ማህበራዊና ፓለቲካ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ ቅድሚያ የጤና ልማት ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለዚህ በዘርፉ የምስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የተሻለ የጤና አገልግሎቶች መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል ።
በባለፍት ዓመታት የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ ተግዳሮቶችን በማለፍ ጤናን መሠረት ያደረጉ ስራዎችን በመስራት ዘርፌ ብዙ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደምገኙ ጠቁመው ለዚህም የጤና ባለሙያዎች ቁርጠኛ ስለ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
የጤናው ዘርፍ አርበኝነት ለሀገር ዕድገት በምል መነሻ ሀሳብ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራአስኪያጅ በአቶ አስታውሰኝ አደሎ እንደ ሀገር በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶቻችንና ያጋጠመው ችግሮችን በስፍት አንስተዋል ።
በቀረበው ሰነድ መነሻ ሀሳባቸውን የሰጡት የሆስፒታሉ ሰራተኞች በበኩላቸው የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ጨምሮ የትራንስፖርትና ሌሎችም አገልግሎቶች እንድሟላ ጠይቀው የስራ ቦታዎችን ሚቹ ከማድረግ አንፃር ትኩረት ልደረግ እንደምገባ ተናግረዋል ።
የእናቶች ማቆያ፣ የካፌ አገልግሎቶችና ሌሎች መሟላት የምገቡ ነገሮች እንድሟሉ የጠየቁት ሰራተኞቹ ከተጠቃሚዎች ቁጥር አንፃር ሆስፒታሉን የማስፋት ስራዎች ላይ ትኩረት ልሰጥ ይገባል ብለዋል።
ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የዞን አስተዳዳሪን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥቶባቸው መሻሻል በምገቡ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል ።
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳብ አቶ አበበ ማሞ ፣ የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፍ አቶ እምሩ ወዬሳን ጨምሮ የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ አስቻለው አየለ
More Stories
በተገባደደዉ የበልግ አዝመራ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የእንሰት ችግኝ መትከሉን የአንድራቻ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለዲጅታል ማንነት ያስተላለፉት መልዕክት፦
አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ተባለ።