May 15, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ እንዲፈጠር የምግብ -ስርዓትና ስርዓተ – ምግብ ትግበራዎችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ

ማሻ ፣ የግንቦት 07፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ ብዝሃ ሴክተር የ 9 ወራት የአፈጻጸም ግምገማ ተደርጓል ፡፡

በአፈጻጸም ግምገማው የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ በአዕምሮ የበለጸገ ትውልድ እንዲፈጠር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ያልተመጣጠነ አመጋገብን ማሻሸል በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል ፡፡

በምግብ ስርዓትና በሰቆጣ ቃል ኪዳን የሚከናወኑ ተግባራት በክልላች የህጻናትን የመቀንጨር ምጣኔ ለመቀነስ ዓይነተኛ የመፍተሄ አቅጣጫ ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ንጉሴ ተባባሪ ተቋማት ተግባሩን በሚፈለገው መንገድ ውጤታማ እንዲሆን የጀመሩትን ተግባር ማጠናከር እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡

ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በ2030 13% የመቀንጨር ምጣኔ ለመቀነስ ከ2 ዓመት በታች የመቀንጨር ምጣኔን ወደ ዜሮ ለማውረድና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተሰባጠረ አመጋገብ እንዲኖራቸው ለማስቻል ባለፉት 9 ወራት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል ፡፡

በክልላችን የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ እንዲሁም የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባራት እስከ ማህበረሰብ ድረስ ለ4 ተከታታይ ዓመት እየተሰራ መቆየቱንና ለውጦች መኖራቸውን አቶ ማቴዎስ ገልጸዋል ፡፡

በምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ከክልል ጀምሮ እሰከ ቀበሌ ደረጃ የምግብና ስርዓተ ምግብ አማካሪ ምክር ቤት በማቋቋም በባለቤትነት በ17 ወረዳዎች በ124 ቀበሌዎች ስራው እየተመራ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡

በበተሰብ ደረጃ በእርሻ ምርት በስርዓተ ምግብ የበለፀገ ምርትን በአፈጻጸሙ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በሪፓርቱ በተነሱ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ በቀጣይ አትኩሮት ሊሰጥ እንደሚገባም አንስተዋል።

የስርዓተ ምግብ ተግባራት ህዝባዊ መሰረት ለማስያዝ የማስገንዘብ እና የማሳወቅ ስራ ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል።

የቴክኒክ ኮሚቴና ፎካሎች ተግባራቸውን መወጣት ፣ የማቺንግ ፈንድ በተገቢው መመደብ፣ የሪፓርት አላላክ በጊዜና ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንደሚገባም ተነስቷል።

በአፈጻጸም ግምገማው የክልሉ የምግብና ስርዓተ ምግብ አማካሪ ምክርቤት አባላት፣ የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪዎች፣የየተቋማቱ ፎካል ፐርሰኖች፣የዞን አስተዳዳሪዎችና የጤና መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ፡፡

ክልል ኮሚኒኬሽን