ማሻ ፣ የግንቦት 05፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ስምምነቶችን ተፈራረመ፡፡
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ፎረም ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡
በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለኢንቨስትመንት በቁርጠኝት እየሠራ መሆኑ በስፋት መነሳቱ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በግብርናና አግሮፕሮሰሲንግ፣ በማምረቻ፣ በአገልግሎት፣ በአይሲቲ እና በሌሎችም ዘርፎች ከፍተኛ አቅም እንዳላት ያሳየችበት መድረክ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡
በሀገሪቱ የተወሰዱ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችም ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ወሳኝነት ያላቸው መሆኑን አብራርተዋል።
ፋና
More Stories
ሚኒስቴሩ ለሦስት ኩባንያዎች የማዕድን ምርት ፍቃድ ሰጠ
በክልሉ ከሚገኙ ቡና አቅራቢ ነጋዴዎች ጋር በወቅታዊ የቡና ገበያ ላይ በቦንጋ ከተማ ምክክር እየተደረገ ነዉ
የጣሊያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያጠናከሩ ተጠየቀ፡፡