ማሻ ፣ የግንቦት 03፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) እናቶች ስሰለጡን ፍቅር፣ ስለዋሉልን ውለታ፣ ስለከፈሉት መስዋዕትነት የምንዘክርበት የእናትነት ቀን ዛሬ በዓለም አቀፋ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
ልቧን፣ ህይወቷን፣ ጉልበቷን፣ ጤናዋን፣ ጊዜዋን፣ ሀብቷን ሰጥታ በፍቅር ያሳደገችን የመጀመሪያ ትምህርት ቤታችን የእናትን ውለታዋን በቃላት መግለፅ ከባድ ነው።
እናቶች የማይቻለውን ችለው፣ ማንም የማይከፍለውን ዋጋ ከፍለው፣ ምንም ዓይነት ፈተና ሳይበግራቸው በፅናት ልጆችን የማሳደግ ትልቁን ኃላፊነት በጥንካሬና በጀግንነት እየተወጡ ይገኛሉ።
የእናትነት ቀን የሚከበረው በዋናነት ወልደው ላሳደጉን እናቶች እውቅና ለመስጠት ቢሆንም፤ የእንጀራ እናቶች፣ ሴት አያቶች እና ሌሎች እንደ እናት የማሳደግ ሚናን የተወጡ ሴቶችን ጭምር የሚያካትት ነው።
የእናቶች ቀን ሲከበር ታዲያ ሁሉን ሰጥተው፣ ሁሉን አድርገው ላሳደጉን እናቶች ምስጋናችንን እና ፍቅራችንን ለመግለጽ መፃሕፍትን እና በእጅ የተሰሩ የእደ ጥበብ ውጤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎችን በማበርከት ነው።
ምግብ ማብሰልን በመሳሰሉ በተለያዩ ተግባራት እናቶችን በመርዳት በቂ እረፍት እንዲያገኙ ማገዝም የአከባበሩ አካል ነው።
ቀኑ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በፎቶ እና በተንቀሳቃሽ ምስል ለእናቶች አበርክቶና ውለታ ተገቢውን ክብር በመስጠት ጭምር ይከበራል።
ሁሉም እናቶች የተሻለ የጤና አገልግሎትና የወሊድ ፈቃድ እንዲያገኙ በማድረግ በህብረተሰቡ ውስጥ ላላቸው የላቀ ዋጋ እውቅና የሚሰጥበትም ነው።
በየማህበረሰቡ ውስጥ በእናቶች የሚመሩ የንግድ ሥራዎችና የበጎ አድራጎት ተግባራት ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት የሚደረግበትም ነው የእናትነት ቀን ።
More Stories
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በሩሲያ የድል በዓል የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ ተሳተፉ
አሜሪካዊው ሮበርት ፕሪቮስት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመረጡ