May 12, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በዞኑ ከ48 ሺህ 3መቶ በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ገለፀ።

ማሻ ፣ የግንቦት 04፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) መምሪያው የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻን ለማሰጀመር ዓላማ ያደረገ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ አካሂዷል ።

የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ እምሩ ወዬሳ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የክትባት ዘመቻው ውጤታማ እንድሆን ለዘርፍ ባለሙያዎች ስልጠና ከመስጠት በተጨማሪ አስፈላጊ የሆኑ ግባቶችን የሟሟላት ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

ከዘመቻው ጎን ለጎን ህብረተሰቡ ጤናውን እንድጠብቅ የግንዛቤ ስራዎች እንደምሰራ የገለፁት ኃላፊው የክትባት ዘመቻው እንዲሳካ የተሽከርካሪና ሌሎች ድጋፎችን እንደምጠይቅ ገልፀዋል ።

የሸካ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ምንተስኖት እንዳሻው በበኩላቸው የዚህ ክትባት ዘመቻ ዕቅድ እንድሳካ በየደረጃው የምገኙ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።

ለዚህም የዞን አስተዳደር የበኩሉን ድጋፍ እንደምያደርግ ጠቁመው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፤ ባለሙያዎች እንድሁም የሀይማኖት አባቶች እና የማህበረሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን እንድወጡ አሳስበዋል ።

በዞኑ ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ 48 ሺህ 3መቶ 38 ህጻናት በጤና ተቋማትና ጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን የሀይማኖት አባቶችና ለሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ዘመቻው እንዲሳካ አስፈለጊውን ድጋፍ እንድያደርጉ ጥር ቀርቧል።

የመከላከያ ክትባት ዘመቻው ከግንቦት 6 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 10 ቀናት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ዘጋቢ አስቻለው አየለ