May 11, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ማሻ ፣ የግንቦት 02፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡

በዚህም መሠረት፦

1ኛ.የ38ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔን መርምሮ አፅድቋል።

2ኛ.በመቀጠልም የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል።በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን 11 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን፦9 የግብርና እና 2 የአገልግሎት የስራ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት 847 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ የቀረቡ ኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።

3ኛ.የገጠር ተደራሽ መንገድ የአጭር ጊዜ የቁርጥ ዋጋ ተመን ማሻሻልን የተመለከተ አጀንዳ ላይ ተወያይቶ የቀረበዉ ጥናት ወደ ሥራ እንዲገባና በጥንቃቄ እንዲፈጸም ተወስኗል።

4ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በተለያዩ ረቂቅ ደንቦችና አንድ መመሪያም ላይ ተወያይቷል። በዚህም

ሀ.የገቢ አሰባሰብ፣አስተዳደር እና አጠቃቀም ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ወደ ስራ እንዲገበ ወስኗል።

ለ.የገጠር መጠጥ ዉሃ ሳኒቴሽን ማህበራት ማቋቋሚያ የወጣ ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

ሐ. ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈል ካሳ እና የልማት ተነሺዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም የወጣ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ተወያይቶ ሥራ ላይ እንዲዉል ምክር ቤቱ ወስኗል።

ክልል ኮሚኒኬሽን