ማሻ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ80ኛው የሩሲያ የድል በዓል ለሚሳተፉ የሀገራት መሪዎች ማምሻውን በክሬምሊን ቤተ መንግስት በተካሄደው የአቀባበልና የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ ተሳትፈዋል።
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በድል ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ለመጡ የሀገራት መሪዎች አቀባበል አድርገዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የድል በዓሉ 2ኛው የዓለም ጦርነት ማብቃቱን ተከትሎ በተለይም የቀድሞው ሶቪየት ኅብረት ጦር የተቀዳጀውን ድል በማሰብ በሞስኮ የቀይ አደባባይ የሚካሄደውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትርኢት ጨምሮ ሌሎች መርሃ ግብሮች ይከናወናሉ።
More Stories
የኢትዮጵያ መንግሥት የ3.5 ቢሊዮን ዶላር የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ተፈራረመ
በግብርናው ዘርፍ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ አለባት የሚል ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የ2018 የፌዴራል መንግሥት በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ