ማሻ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ቼልሲ እና ሪያል ቤቲስ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት የፍጻሜ ተፋላሚ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ የስዊድኑን ዩርጋደን ያስተናገደው ቼልሲ 1 ለ ዐ (በድምር ውጤት 5 ለ 1) በመርታት ለፍጻሜ ማለፍ ችሏል፡፡
በሌላ ጨዋታ ፊዮረንቲና ሪያል ቤቲስን 2 ለ 1 ማሸነፉን ተከትሎ በደርሶ መልስ ውጤት 3 ለ 3 አቻ በመለያየታቸው ሁለቱ ክለቦች ወደ ጭማሪ ደቂቃ አምርተዋል።
በተጨማሪ ደቂቃ ሪያል ቤቲስ ጎል አስቆጥሮ በድምር ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
More Stories
ማንቼስተር ዩናይትድና ቶተንሃም ለዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ አለፉ
ቼልሲ ሊቨርፑልን አሸነፈ
ባየርን ሙኒክ የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን ሆነ