ማሻ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድና ቶተንሃም ሆትስፐር ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት የፍጻሜ ተፋላሚ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ የስፔኑን ክለብ አትሌቲክ ቢልባኦ ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 4 ለ 1 (በድምር ውጤት 7 ለ 1) በመርታት ለፍጻሜ ማለፍ ችሏል፡፡
የዩናይትድን ግቦች ሜሰን ማውንት (2)፣ ካሴሚሮ እና ራስሙስ ሆይሉንድ አስቆጥረዋል።
ሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር ወደ ኖርዌይ በማቅናት ቦዶ ግሊምትን 2 ለ ዐ (በድምር ውጤት 5 ለ 1) በመርታት የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ከ2 ሳምንት በኋላ በስፔን ቢልባኦ በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ በቀጣዩ አመት የሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
More Stories
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
ቶትነሃም ከ17 አመታት በኃላ ዋንጫ አነሳ፣ የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊነቱንም አረጋገጠ
54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ