May 5, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ባየርን ሙኒክ የቡንደስሊጋው ሻምፒዮን ሆነ

ማሻ፣ ሚያዝያ 26፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ባየርን ሙኒክ የ2024/25 የጀርመን ቡንደስሊጋ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

ዛሬ በተካሄደው የ32ኛ ሳምንት የቡንደስሊጋው መርሃ ግብር 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ባየር ሊቨርኩሰን ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ባየርን ሙኒክ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት የሊጉ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

እንግሊዛዊው አጥቂ ሀሪ ኬን የመጀመሪያውን ዋንጫ ከባቫሪያኑ ጋር ማሳካት ችሏል።