ማሻ፡ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የይዘት ዘርፍ ኃላፊ የተመራ የማናጅመንት ቡድን በማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ ያለውን አደረጃጀት እና አፈጻጸም ምልከታ አድርጓል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የድርጅቱ ተወካይ አቶ ዘላለም ገነሞ 12ኛ ቅርንጫፍ ሆኖ በአጭር ጊዜ የተቋቋመውን የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ ያለበትን የይዘትና አጠቃላይ አሰራር ሂደትን የጎበኙ ሲሆን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለሸካ ዞንና ለአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጭምር የመረጃ ምንጭ በመሆኑ ይህም የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ተቋማዊ ግንኙነትን በማጠናከር ተከታታይነት ያለው ድጋፍ እንደሚቀጥልና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከዋናው መስሪያ ቤት፣ ከክልሉ መንግስት እና ከዞኑ አስተዳደር ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
በቴክኖሎጂ የታገዘ ግንኙነት በማድረግ የተጀመረውን ተቋማዊ አሰራር ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መሆኑን በዋናው ጣቢያ የሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተወካይና የስቱዲዮ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ታምሩ አስረድተዋል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ናማሮ በበኩላቸው፤ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች የተናበበ ስራ ለመጣው ለውጥ አቅም መሆኑን አመላክተው ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የሚዲያ ተደራሽነትና የዜጎች መረጃ የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብት ምላሽ እንዲያገኝ ከማድረግ አኳያ ቅርንጫፉን ማደራጀት መቻሉን የጠቆሙት የጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ጎዱ፥ የዞኑ አስተዳደር በራስ አቅምና ሌሎች አጋዥ አካላት ላደረጉት ቀና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በተቋሙ የዋናው መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ታምሩ፥ ዋናው መስሪያ ቤት ለቅርንጫፍ ጣቢያው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
More Stories
በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ ።
ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ሁለተኛውን የዓርበኝነት ምዕራፍ ጀምራለች – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ላለው ፈጣን እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፦ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር)