May 2, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ማንቼስተር ዩናይትድ አትሌቲክ ቢልባኦን አሸነፈ

ማሻ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ አትሌቲክ ቢልባኦን 3 ለ ዐ አሸንፏል።

ለማንቼስተር ዩናይትድ የማሸነፊያ ግቦቹን ካሴሚሮ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ (2) አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ከቢልባኦ በኩል ተከላካዩ ቪቪያን በመጀመሪያው አጋማሽ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።

በሌላ የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ የኖርዌዩን ቦዶ ግሊምት 3 ለ 1 አሸንፏል።

በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ቼልሲ በጄደን ሳንቾ፣ ማዱኬ እና ጃክሰን (2) ግቦች የስዊድኑን ዩርጋደን 4 ለ 1 አሸንፏል።

በሌላ የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ ሪያል ቤቲስ ፊዮሬንቲናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የዩሮፓ ሊግ እና የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የመልስ ጨዋታዎች በቀጣዩ ሳምንት ሀሙስ የሚደረጉ ይሆናል።