May 1, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

ሚያዝያ 23፣ 2017 በ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ዛሬ ረፋድ ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ፥ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች በፍቃዱ አለማየሁ እና አንተነህ ተፈራ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 42 በማድረስ ወደ 2ኛ ደረጃ ከፍ ሲል፥ ሽንፈት ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ29 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በሌሎች የዛሬ መርሐ ግብሮች ቀን 9 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም ምሽት 12 ሰዓት መቐለ 70 እንደርታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡