ማሻ ፣ የመጋቢት 16፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) ይህን የገለፁት የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 22ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ነው።
ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎአቸውን በማጠናከር ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ መሰራቱን የተናገሩት አቶ አበበ ከ2ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የብድር አገልግሎት በማመቻቸት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ማሳደግ እንዲችሉ ተሰርተዋል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ ሴቶች ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሚ እንዲችሉ፣የትምህር እድል እንዲያገኙ፣የገጠር መሬት ባለበት እንዲሆኑና ለሎች ዘርፎች ተሳታፍ እንዲሆኑ መሰራቱንም ተናግረዋል።
የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ መቀነስ ፣የህፃናት ተሳትፎ ማሳደግና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን አቶ አበበ ጠቁመዋል ።
ወጣቶችን በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ ገንዘብ ከቆጠቡት 4 ሺህ 3 መቶ በላይ ወጣቶች መካከል ለ1ሺህ 225 ወጣቶች የብድር አገልግሎት ተመቻችቶ ወደስራ መግባታቸውን ተናግረዋል ።
አካል ጉዳተኞች ፣አረጋዊያን ፣በህፃናት የሚመሩ ቤተሰቦችና ፅኑ ህሙማን ከ683 በላይ ዜጎች በገጠርና ከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ታቅፈው ወርሃዊ የገንዘብ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የአካል ጉዳተኞችን ተካታችነት፣ተሳትፎና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት አቶ አበበ 280 አካል ጉዳተኞችን በጤና፣በትምህርት እንዲሁም በተለያዩ መረሃ-ግብሮች ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል ።
በበጀት አመቱ በ6 ወራት የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስጠበቅ በቀጣይ ጊዜያት በሁሉም ዘርፎች የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
More Stories
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል