መጋቢት 14፣ 2017 ኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት በቻይና ናንጂንግ ሲካሄድ በቆየው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም 3ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን አጠናቀቀች፡፡
ሻምፒዮናው ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በውድድሩ 2 የወርቅና በ3 የብር ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡
በሴቶች 3 ሺህ ሜትር አትሌት ፍረወይኒ ኃይሉ እንዲሁም በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
አትሌት በሪሁ አረጋዊ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር፣ አትሌት ድርቤ ወልተጂ በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር እንዲሁም አትሌት ንግስት ጌታቸው በሴቶች 800 ሜትር ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡
በውድድሩ አሜሪካ በ6 የወርቅ፣ 4 የብር እና 6 የነሃስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ÷ ኖርዌይ በ3 የወርቅ እና 1 የነሃስ ሜዳሊያ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።
More Stories
ትዕግስት አሰፋ በዓለም አቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝገብ እውቅና ተሰጣት
ኢትዮጵያ በፊፋ ደረጃ 147ኛ ሆናለች
ኬቨን ዲብሮይን በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ