ማሻ ፣ የመጋቢት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው መርዓዊ ሥጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ክላርኔት በመጫወት የሚታወቀው አርቲስት መርዓዊ፤ ከሙዚቀኛነቱ ባለፈ በትወና መድረክ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሏል፡፡
አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ቦታ ከሚይዙ አንጋፋ ሙዚቀኞች መካከል አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡
ከ55 ዓመታት በላይ በቆየበት የሙዚቃ ሕይዎቱ፤ በድምጻዊነት፣ በክላርኔትና አልቶ ሳክስ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነት፣ በሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲነት እንዲሁም በአቀናባሪነት እና ሌሎች ተዘርፎች ማገልገሉ ይታወሳል፡፡
ፋና
More Stories
በመስክ ምልከታው የተገኘው ልምድ የሌማት ትሩፋት አካል በመሆኑ አርሶ አደሮቻችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል፦
የኢራን አዲሱ መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ …
የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ባለቤትነት ጥያቄ ለቀጣናዊ ሰላም ያለው ፋይዳ