ማሻ ፣ የመጋቢት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም ) በሁቲ አማጺያን በቀይ ባህር ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ካልቆመ አካባቢውን ገሃነም እናደርገዋለን ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዝተዋል::
የሁቲ አማጺያን በቀይ ባሕር መርከቦች ላይ ላደረሱት ጥቃት አሜሪካ ከባድ የአየር ድብደባ ማካሄዷን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ የትስስር ገጻቸው ገልፀዋል::
በድብደባው 15 ሰዎች መገደላቸውንና ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን በሁቲ የሚመራው የጤና ሚኒስትር አስታውቋል።
በሰንአ እና ሳዳ አካባቢ ተከታታይ የአየር ጥቃት ሲሰማ መዋሉንም ቢቢሲ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንቱ በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጺያን በአሜሪካ መርከብ ላይ የሚሳዔል ጥቃት አድርሰዋል ብለዋል::
በጥቃቱም ወታደሮቻቸውና አጋሮቻቸው ዒላማ መሆናቸውን ገልፀዋል::
እስከአሁን በሁቲ አማጺያን የሽብር ድርጊት በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት አጥተናል፤ ሕይወትም አደጋ ውስጥ ወድቋል ብለዋል።
አሜሪካና አጋሮቿ ቀይ ባሕር ላይ የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል ኃይል ቢያሰማሩም ማስቆም ግን አልቻሉም።
ሁቲዎች እጃቸውን ካልሰበሰቡ አካባቢውን ገሃነም እናደርገዋለን ሲሉ ትራምፕ ዝተዋል::
ሁቲ በምላሹ የአሜሪካ የአየር ጥቃት አሜሪካና አጋሮቿን ከባድ ዋጋ ያስከፍላል ብሏል::
ኢራን በጉዳዩ ስሟ መነሳቱ አላስደሰታትም::
ፋና
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ