ማሻ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ማንቼስተር ዩናይትድ 100 ሺህ ተመልካቾችን የሚያስተናግድ አዲስ ግዙፍ ስታዲየም ሊገነባ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
በሁለት ቢሊየን ፓውንድ ወጪ የሚገነባው አዲሱ ስታዲየም በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃልም ነው የተባለው፡፡
ክለቡ ለ115 ዓመታት ያህል ሲገለገልበት ከቆየው ኦልድትራፎርድ አቅራቢያ የሚገነባው አዲሱ ስታዲየም እስከሚጠናቀቅ ድረስ በዛው በኦልድትራፎርድ ጨዋታዎቹን እንደሚያከናውን ተገልጿል፡፡
ክለቡ ይፋ ባደረገው ዲዛይን መሰረት ስታዲየሙ እያንዳንዳቸው 200 ሜትር ከፍታ ያላቸው ሶስት ምሶሶዎች እንደሚኖሩትም የቢቢሲ ስፖርት ዘገባ አመላክቷል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ
የአዲሱ ስታዲየም ፕሮጀክት ይፋ ከመደረጉ በፊት ነባሩን ኦልድትራፎርድ ማደስ አልያም አዲስ ስታዲየም መገንባት በሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት ሲደረግ መቆየቱንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
More Stories
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
ቶትነሃም ከ17 አመታት በኃላ ዋንጫ አነሳ፣ የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊነቱንም አረጋገጠ
54ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ