የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በጉባዔዉ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ምክርቤቱ ባለፉት 6 ወራት በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት የተለያዩ ጥረቶች ማድረጉን ተናግረዋል ፡፡
የክልሉ ምክር ቤት ከፍተኛ የህግ አውጭ አካል በመሆኑ የፌዴራሉን ህገ መንግስት በማይጻጸር መልኩ በክልሉ ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆኑ ህጎችን የማውጣት፣የአስፈጻሚ አካላትን ተግባር የመከታተልና የመቆጣጠር ስራዎችን ሲከናውን መቆየቱን አፈ ጉባኤ ወንድሙ ተናግረዋል ፡፡
ምክር ቤቱ በ6 ወራት ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ማከናወን መቻሉን የገለጹት ዋና አፈ ጉባኤው በኦዲት ስራዎች ላይ በኦዲት ግብረ ሀይል ስራዎችን በመገምገምና አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ መቻሉን ተናግረዋል ፡፡
በጉባኤው የ6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ረቂቅ ቃለ ጉባኤን መርምሮ ማጽደቅ፣የአስፈጻሚ አካላት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ፣ከተቋማት የቀረቡ አዋጅና ደንድ መርምሮ ማጽደቅ፣የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔት ዎርክ የ2017 በጀት ዓመት የ6ወራት የስራ ዕቅድ መርምሮ ማጽደቅ እና ልዩ ልዩ ሹመቶችን መርምሮ ማጽደቅ የጉባኤው አጀንዳ እንደሆኑም ታውቋል ፡፡
ክ/መ/ኮ/ጉቢሮ
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ