ማሻ፣ ጥር 29፣ 2017 (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ብራዚላዊው የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ማርሴሎ ከእግር ኳስ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡
የግራ መስመር ተከላካዩ ማርሴሎ በሪያል ማድሪድ ቤት ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን 5 የሻምፒዮንስ ሊግ እና 6 የላሊጋ ዋንጫዎችን ከሎስ ብላንኮቹ ጋር ማንሳት ችሏል፡፡
ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 58 ጊዜ ተሰልፎ በመጫዎት 6 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል፡፡
ከሪያል ማድሪድ በመውጣት በግሪኩ ኦሎምፒኮስ እና በብራዚሉ ፉለሉሜንሴ ያልተሳካ ጊዜያት ያሳለፈው ማርሴሎ ከደቂቃዎች በፊት በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በይፋ ጫማ መስቀሉን አስታውቋል፡፡
(ኤፍ ኤም ሲ)
More Stories
አንድሬ ኦናና ከቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታዎች ውጪ ሆነ
ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ