አሁን ላይ ከእንሰት ተክል አስተዋፅኦዎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ምክንያት በዘርፉ ጥናትና ምርምሮች እየተከናወኑ መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በዚህም እንሰት ለምግብነትና ለተለያዩ የቤት ቁሳቁስ ሆኖ ከመዋል አልፎ ተረፈ ምርቱ በፋብሪካ ውስጥ ገቢቶ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ በመሆኑ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ተስጥቶ እየተሰራ ይገኛል።
የአንድራቻ ወረዳ እርሻ፣ደን፣አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ፅ/ቤት በበጀት ዓመቱ 12 ሚሚልዮን የእንሰት ችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝግጂት እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ሸነኖ ከባለፈው አመት ጀምሮ የችግኝ ዝግጅት እንዲደረግ ከአርሶ አደሮች ጋር በመግባባት ሰፋፍ ስራዎች ስሰሩ መቆየቱን አመላክተዋል።
በተያዘው አመት የተጣለውን ግብ ለማሳካት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ልደግፉና በጋራ መስራት እንደሚገባም ጽ/ቤቱ አሳስበዋል።
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …