የሸካ ዞን ግብና አከባቢ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ አቶ አእምሮ ደሳለኝ የ2017 ዞናዊ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት መርሃ-ግብር በዞኑ በተለዩ 59 ንዑስ ተፋሰሶች ከ17 ሺህ 9 መቶ 13 ሄክታር መሬት በላይ ለመሸፈን ግብ ተጥሎ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
የዘንድሮው የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ከ2016 ዓ/ም ተሞክሮዎች ተቀምረው የሚተገበሩበት መሆኑን የጠቆሙት አቶ አእምሮ ከዓምናው ስራዎች በተለይም በእንስሳት መኖ፣ በእርከን ስራ፣ በእንሰትና የሙዚ ተክል የተሻለ ስራ እንደተሰራም ገልፀዋል።
የተፈጥሮ ሀብታችንን በቅንጅት የመጠበቅ እና የመንከባከብ ጉዳይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት የጠቀሱት የመምሪያው ኃላፊው “የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል በዞን ደረጃ የ2017 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ እንደሚተገበር ጠቁመዋል።
በዞን ደረጃ በየኪ ወረዳ ዚንኪ ቀበሌ የማስጀመሪያ መርሃ -ግብር የተከናወን ስሆን በተመሳሳይ በሁሉም ወረዳዎች እንደተጀመረ ገልጸው በዘንድሮው የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ላይ ከ60 ሺህ 5መቶ በላይ ህዝብ በ1ሺህ 5መቶ 29 የልማት ቡድን እንደሚሳተፍ አመልክተው ።
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ