በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ የተቀበሉት አሜሪካዊው ሴናተር የ11 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ የተቀበሉት የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ቦብ ሜኔንዴዝ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የዓይነት ጉቦ መቀባላቸው በመረጋገጡ ነው እስራቱ የተፈረደባቸው።
በተለይም ከግብፅ መንግሥት የተቀበሏቸው ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብ እና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና ለወንጀላቸው ማረጋገጫ ተደርገው ለፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ሜኔንዴዝ በጠበቃቸው በኩል ቀለል ያለ የማኅበራዊ አገልግሎት ቅጣት እንዲጣልባቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ግን የ11 ዓመታት እስራት ፈርዶባቸዋል።
በተያያዘም ረቡዕ ዕለት ሁለት የሜኔንዴዝ ተባባሪዎች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
በኒው ጀርዚ የሪል እስቴት አልሚ የሆነው እና ለሴናተሩ ወርቅ እና ጥሬ ገንዘብ እንደሰጠ የተነገረለት ፍሬድ ዳይቤስ የ7 ዓመት እስራት እና 1.75 ሚሊዮን ዶላር ተቀጥቷል።
ሜኔንዴዝን ከግብፅ መንግሥት ጋር በማገናኘት ወንጀል የተሳተፈ ዋኤል ሃና የተባለ ግብጻዊ-አሜሪካዊ ነጋዴም ከስምንት ዓመት በላይ እስራት እና የ1.25 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ተወስኖበታል።
ኢቢሲ
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ