2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ በመጪው ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ካሉ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እንዲመዘገቡ ያሳሰበው አገልግሎቱ፤ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ፈተናውን እንደማይፈተኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት አስጠንቅቋል።
EBC
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ